ኢትዮጰያ ህዳሴ ግድብን በድል ማጠናቀቋ ሌሎች የላቁ ኘሮጀክቶችንም መስራት እንደምትችል ለአለም ህዝብ ያረጋገጠችበት መሆኑ ተገለፀ‎

You are currently viewing ኢትዮጰያ ህዳሴ ግድብን በድል ማጠናቀቋ ሌሎች የላቁ ኘሮጀክቶችንም መስራት እንደምትችል ለአለም ህዝብ ያረጋገጠችበት መሆኑ ተገለፀ‎

‎AMN -ሀምሌ 11/2017 ዓ.ም

‎ኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ኘሮጀክትን በድል ማጠናቀቋ ሌሎች ግዙፍ ኘሮጀክቶችንም በራሷ አቅም መገንባት እንደምትችል ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ያሳየችበት ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ከ ኤ ኤም ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

‎የህዳሴ ግድብን በተመለከተ በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ኢትዮጵያ የተከተለችው ጠንካራ እና ጥበብ የተሞላበት ዲኘሎማሲያዊ አካሄድ ግድቡን በድል አድራጊነት እንድታጠናቅቅ አስችሏታል ብለዋል፡፡


በተለይም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በፀጥታው ምክር ግድቡን በተመለከተ የተለያዩ ክሶች የቀረቡበትን ወቅቶች ያስታወሱት አምባሳደሩ፣ ነገር ግን በበሳል ዲፕሎማሲ ኢትዮጵየ በግድቡ ዙሪያ የያዘችውን እውነት በማስረዳትና ለቀጠናው ብሎም ለአፍሪካ የሚኖረው አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደሆነ በማስገንዘብ ዓለምን በብዙ መልኩ ለማሳመን ያደረገችውን ወሳኝ ጥረት በአብነት አንስተዋል፡፡፡

አንዳንድ አገሮች በቅኝ አገዛዝ ዘመን የነበሩ ስምምነቶችን በመምዘዝና አንቀፆችንም በመጥቀስ ተጨባጭ ያልሆኑንና ከእውነታው የራቁ ሙግቶችን በማቅረባቸው ኢትዮጵያን ከጉዞዋ ሊያስቆሙ እንዳልቻሉ አስገንዝበዋል፡፡


‎አሁን ግድቡ ተጠናቆ ሪቫን መቁረጥ ብቻ የቀረው ጉዳይ መሆኑን አንስተው ከዚህ ጎን ለጎንም በስፋት እየተሰራበት ያለው የአረንጎዴ አሻራ ሥራ ለግድቡ ትልቅ አስተዋፅዖ የሚያበረክት እንደሚሆን አምባሳደሩ በቆይታቸው አብራርተዋል፡፡

በሔለን ተስፍዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review