በከተማዋ የትምህርት ተደራሽነት እና ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ፕሮጀክቶች መገንባታቸው ተገለፀ

You are currently viewing በከተማዋ የትምህርት ተደራሽነት እና ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ፕሮጀክቶች መገንባታቸው ተገለፀ

AMN- ሐምሌ 11/2017

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በመንግሥት እና በማህበረሰብ ተሳትፎ የተገነቡ ማስፋፊያ የተደረገላቸው ትምህርት ቤቶች ተመርቀዋል።

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በመንግስትና በማህበረሰቡ ተሳትፎ የተገነቡ የማስፋፊያ ግንባታ የተደረገላቸው ትምህርት ቤቶች የምረቃ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጥራቱ በየነ፣ የትምህርት ተደራሽነት እና ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ፕሮጀክቶች መገንባታቸውን ገልፀዋል፡፡

መጪው ትውልድ በአካል፣ በሥነ ልቦና፣ በእውቀት እና በክህሎት ብቁ እንዲሆኑ የሚያግዙ ተግባራት ተከናውነዋል ያሉ ሲሆን፣ ይህም ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ዘርፍ የሰጠውን ትኩረት የሚያሳይ ነው ብለዋል።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ በበኩላቸው እነዚህ የትምህርት መሰረተ ልማቶች የነገውን ትውልድ መገንቢያ ናቸው ብለዋል።

ለትምህርት ተቋማት የተሰጠው ትኩረት የተማሪ ክፍል ጥምርታን በማሻሻል ረገድም ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንደሚያበረክት ተናግረዋል፡፡

በክፍለ ከተማው የተመረቁት ትምህርት ቤቶች የስፖርት ሜዳዎች እና ቤተ መፅሀፍትን ጨምሮ የመመገቢያ አዳራሾችን ያካተቱ ናቸው።

በመሀመድኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review