በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኪልባቲ ራሱ ዳሎል ወረዳ ባዳ አድማሩግ ቀበሌ ትናንት ከቀኑ 10፡00 ላይ የእሳት ቃጠሎ አደጋ መከሰቱን የዳሎል ወረዳ አስተዳዳሪ ኢስማኤል አሊ ለኤ ኤም ኤን ተናግረዋል፡፡
በአደጋው ከ20 በላይ የቤት እንስሳት መሞታቸውን የገለፁ ሲሆን 600 ሱቆች፣ 950 ምግብ ቤቶች እና 255 መኖሪያ ቤቶች፤ በጥቅሉ ከ1ሺህ 800 በላይ ቤቶች ወድመዋል ነው ያሉት፡፡
በአሁኑ ሰዓት በህብረተሰቡና በመንግስት ጥረት አደጋውን 95 በመቶ መቆጣጠር መቻሉን ተናግረዋል።
አካባቢው ከባድ ንፋስ ያለበት በመሆኑ እሳቱን የመቆጣጠር ሥራ ፈተኝ አድርጎት እንደነበር አስታውቀዋል፡፡
የአብዓላ ሆስፒታል፣ ባራህሌ ሆስፒታል እና ሌሎች የጤና ባለሙያዎች የህክምና ቁሳቁሶችን ለህብረተሰቡ እያቀረቡ እንደሚገኙ ተናግረዋል::
የባራህሌ ወረዳ አስተዳደር እና ህብረተሰቡ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረጉ መሆኑንም ተናግረዋል።
በአብዱ መሀመድ