አዲስ አበባ አብዛኛው በጀቷን ሰው ተኮር ለሆኑ ፕሮጀክቶች እያዋለች እንደምትገኝ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን ተናገሩ

You are currently viewing አዲስ አበባ አብዛኛው በጀቷን ሰው ተኮር ለሆኑ ፕሮጀክቶች እያዋለች እንደምትገኝ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን ተናገሩ
  • Post category:ልማት

AMN- ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ አብዛኛው በጀቷን ሰው ተኮር ለሆኑ ፕሮጀክቶች እያዋለች እንደምትገኝ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን ተናግረዋል፡፡

የከተማ አስተዳድሩ 5 ቢሊየን ብር የወጣባቸውን ትምህርት ቤቶች አስመርቋል፡፡

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፕሮጀክቶችን ያስመረቁት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን፣ እንደ ከተማ አዳዲስ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውንና የማሻሻያ ግንባታ ስለመከናወኑ ጠቅሰዋል፡፡

ታዳጊዎች ላይ በስፋት ለመስራት ትምህርት ቤቶችን መገንባት፣ ማዘመንና ማሻሻል የከተማ አስተዳድሩ ተቀዳሚ ተግባራት መካከል መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

በዚህም መሰረት ትምህርት ቤቶችን በመገንባት እና በማሻሻል ለምረቃ ማብቃት ተችሏል ብለዋል፡፡

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ፤ የትምህርት ቤቶች ግንባታ እና ማስፋፊያ ጥራት ያለው ትምህርት ለትውልድ ለመስጠት እና የተማሪ የክፍል ጥምርታ ደረጃውን የሚያስጠብቅ ነው ብለዋል፡፡

በንጉሱ በቃሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review