የጎንደር ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ 2 ሺ 500 በላይ ተማሪዎች አስመረቀ

You are currently viewing የጎንደር ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ 2 ሺ 500 በላይ ተማሪዎች አስመረቀ

AMN-ሐምሌ 12/2017 ዓ/ም

ዩኒቨርስቲው በተመሰረተ በ7ዐኛ ዓመቱ ለ67ኛ ጊዜ ከ2500 በላይ ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

በምረቃ ‎ስነ-ስርዓቱ የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አስራት አፀደወይን እንዳሉት ዩንቨርስቲው ከመማር ማስተማሩ ጎን ለጎን በጥናትና ምርመር ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት አንፃር ትልቅና ዘርፈ-ብዙ ስራዎች ተከናውነዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ዶክተር አስራት አክለውም ‎ከ33 በላይ አዳዲስ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ተቋማት ጋር ግኑኝነት በመመስረት የተቋሙን የልህቀት ማዕከልነቱንና የእውቀት ተደራሽነቱን እያረጋገጠ ይገኛል ብለዋል።

‎ተመራቂዎቹ በስራ ፈጣሪነት እና ከዩኒቨርስቲው ያገኙትን ተጨባጭ እውቀት በመጠቀም ለሀገራቸውን ሁለንተናዊ እድገት አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

‎የትምህርት ሚኒስቴር ተወካይ ዶክተር ሰለሞን አብረሃ እንደገለፁት ሀገሪቱ የትምህርት ዘርፉን ማነቆዎች ለመፍታ ከሪፎርም ጀምሮ ረዥም ጉዞ እያደረገች መሆኑን ጠቅሰው ተመራቂ ተማሪዎች በሳይንስና ቴክኖሎጂ በመተጋገዝ ተወዳዳሪና ሪፎርሙን የሚያግዙ መሆን አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል።

በምረቃ ስነስርዓቱ በማህበረሰቡ በጎ ተፅዕኖ ያሳደሩ፣ ዓለም አቀፍ የመሪነት ሚና ያላቸው፤ በስራ ፈጣሪነትና በአርያነት በሚነሱ ተግባራት ይገባቸዋል የተባሉ ግለሰቦች ተሸልመዋል።

በአፈወርቅ ዓለሙ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review