ከርቀት በሮቦት የተከወነ ቀዶ ጥገና

You are currently viewing ከርቀት በሮቦት የተከወነ ቀዶ ጥገና

AMN – ሐምሌ 12/2017 ዓ.ም

ከቻይና እና ከዩናይትድ ኪንግድም የተሰባሰቡ ሶስት ከፍተኛ የቀዶ ጥገና ባለሞያዎች ታሪክ ቀያሪ የተባለለትን የቀዶ ጥገና ሙከራ አካሂደዋል።

በሻንጋይ ሬንጂ ሆስፒታል መሪነት የተካሄደው ቀዶ ጥገና በአንድ ጊዜ ሻንጋይ፣ ሆንግ ኮንግ እና ለንደን ያሉ የቀዶ ጥገና ባለሞያዎች ባሉበት ሆነው የተሳተፉበት ነው።

ቀዶ ጥገናው በቻይና በተሰራ የቀዶ ጥገና ሮቦት አማካኝነት የአንድ አሳማን የጨጓራ እጢ ማስወገድ የተቻለበት ነው።

የቀዶ ጥገና ሙከራው የተሳካ እንደነበር የገለፁት የቀዶ ጥገና ባለሞያዎቹ አጠቃላይ ሂደቱ በአንድ ቦታ ሆነው ቀዶ ጥገናውን ያከናወኑ ያህል ምቹ እንደነበር ገልፀዋል።

ሙከራው የቻይናን የርቀት የቀዶ ጥገና ሮቦቶች አስተማማኝነት ያሳየ ነው ሲል ቻይና ዴይሊ ዘግቧል።

የጤና ባለሞያዎችም ሙከራውን ታካሚዎችን ማንቀሳቀስ ሳያስፈልግ የሚከወን፤ ለወደፊቱ የርቀት ህክምና ሞዴል የሚሆን ሲሉ አወድሰውታል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review