አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል የተለያዩ የመዝናኛና የንግድ ሁነቶችን ለማዘጋጀት ተመራጭ ስፍራ መሆኑ ተገለጸ

You are currently viewing አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል የተለያዩ የመዝናኛና የንግድ ሁነቶችን ለማዘጋጀት ተመራጭ ስፍራ መሆኑ ተገለጸ

AMN ሃምሌ 12/2017

አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል የተለያዩ የመዝናኛና የንግድ ሁነቶችን ለማዘጋጀት ተመራጭ ስፍራ መሆኑ ተገለጸ፡፡ በማዕከሉ የኬክ ኢክስፖ ተከፍቷል ፡፡

በመዲናዋ ባለፉት ዓመታት በርከታ መሰረተ ልማቶች ተገንብተዉ ለማህበረሰቡ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

ከእነዚህ መሰረተ ልማቶች መካከል አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ከለውጡ ፍሬዎች አንዱ ሲሆን የኮንፍራንስ የኤግዚቢሽን ቱሪዝሙን በማነቃቃት ላይ የሚገኝ ማዕከል ሆኗል ፡፡

ከዚህ ቀደም የተለያዩ ሁነቶችን ለማስተናገድ አስቸጋሪ የነበረውን ሁኔታም የቀየረ ማዕከል እየሆነ መጥቷል፡፡

ማእከሉ ለተዝናኖትና ለግብይት የሚቀርቡ አገልግሎቶችን በማስተናገድ ላይ ሲሆን በማዕከሉ ለሁለት ቀን የሚቆይ የኬክ ኤክስፖም ተከፍቷል፡፡

የኤክስፖው መከፈት ለሕጻናት የመዝናኛ አማራጭ የእረፍት ጊዜያቸውን ከተለመደው ቀን በተለየ እንዲያሳልፉ እንደሚያግዝ በማእከሉ የተገኙ ህጻናት ተናግረዋል፡፡

መርሀ ግበሩ በኢትዮጵያ ብዙም ያልተለመደ ነው የሚሉት የመርሀ ግብሩ ተሳታፊ ወጣቶች እንደነዚህ ዓይነት ኤክስፖዎች ወጣቱ አዳዲስ ነገሮችን እንዲያይ እንደሚያደርግም ተናግረዋል ፡፡

ወላጆቻቸውም ለልጆቻቸው በተመጣጣኝ ዋጋ ጣፋጭ ምግቦችን በማዘዝ እንዲዝናኑና አዲስ ነገርን እንዲያዩ አስችሏልም ብለዋል ፡፡

በመርሀ ግብሩ የተለያዩ የኬክና ጣፋጭ ምርቶችን ያቀረቡ ስለመሆኑ ያነሱት የኤክስፖው ተሳታፊዎች በከተማዋ የተገነባው ማዕከል ለማህበረሰቡ ሁለንተናዊ አገልግሎት በመስጠት የንግድ እንቅስቃሴውን እያነቃቃ መሆኑን ተናግረዋል::

ማእከሉ የኮንፍራንስ ቱሪዝምን የሚያበረታታና በርካታ ሁነቶችን እያስናገደ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ ገመቹ ናቸው፡፡

በጽዮን ማሞ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review