ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የሠላም ንግግር ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን የገለጹት የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ፣ ነገር ግን በዩክሬን የያዝነው ግባችን ሊሳካ ይገባል ብለዋል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቀናት በፊት፣ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ያላትን ችግር በ50 ቀናት ውስጥ ልትፈታ እንደሚገባ አሳስበው፣ ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን ከባድ ቀረጥ እደሚጣልባት ማስጠንቀቂያ አዘል ንግግር ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው ቃል አቀባዩ ይህን የገለፁት፡፡
በኬቭ እና በምዕራብ አጋሮቿ በኩል፣ ሩሲያ የሠላም ንግግሩን አስተጓጉላለች በሚል የሚነሳውን ሀሳብ፣ የሩሲያ ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ውድቅ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ፑቲን የዩክሬን ነዋሪዎችን በሠላማዊ ሁኔታ ማስፈርን አስመልክቶ ያላቸውን አዎንታዊ ፍላጎት ብዙ ጊዜ ገልፀዋል ያሉት ፔስኮቭ፣ ይህ ግን በብዙ ሂደት እና ጥረት የሚመጣ መሆኑን ለጋዜጠኛች ተናግረዋል፡፡
ለእኛ ዋና ነገር በዩክሬን ያለንን ግብ ማሳካት ነው ያለችው ሩሲያ፣ ማንኛውም የሰላም ድርድር ሩሲያ በፈረንጆቹ 2022 የያዘቻቸውን አራት ግዛቶች ለቃ እንድትወጣ በዩክሬን የሚቀርበው ሀሳብ ሩሲያ የማትደራደርበት ቅድመ ሁኔታዋ ሆኗል፡፡
በተጨማሪም ዩክሬን የኔቶ አባል ለመሆን የምታደርገውን ጥያቄ ውድቅ እንድታደርግ እና የታጣቂ ኃይሏን የመገደብ ውሳኔዎችን እንድትቀበል የሚለውም በሩሲያ በኩል የተቀመጡ የሰላም ንግግር ቅድመ ሁኔታዎች ናቸው፡፡
ይሁንና ይህ የሩሲየ ሀሳብ በኪየቭ እና የምዕራብ አጋሮቿ በኩል ተቀባይነት ሳያገኝ ቆይቷል፡፡
ትላንት የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ በዚህ ሳንምንት አዲስ የሠላም ስምምነት እንደሚኖር አስታውቀዋል፡፡
የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን የሠላም ስምምነቱ መቼ እንደሚካሄድ የታወቀ ነገር ባይኖርም ቦታው ግን በኢስታንቡል ከተማ ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡
ቀደም ሲል በኢስታንቡል የተካሄደው የሩሲያ-ዩክሬን የሠላም ድርድር፣ ሀገራቱ በርካታ እስረኞችን እንዲለዋወጡ በር የከፈተ እንደነበር የአር ቲ ኢ ዘገባ ያመለክታል፡፡
በማሬ ቃጦ