በበጀት ዓመቱ በወንጀል ቅድመ መከላከል ላይ በተሰሩ ስራዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገለፀ

You are currently viewing በበጀት ዓመቱ በወንጀል ቅድመ መከላከል ላይ በተሰሩ ስራዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገለፀ

AMN – ሐምሌ 14/2017 ዓ.ም

በ2017 በጀት ዓመት በወንጀል ቅድመ መከላከል ላይ በተሰሩ ስራዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገለፀ።

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ጀምሯል።

በ2017 በጀት ዓመት በመዲናዋ የተካሄዱ አህጉር አቀፍና ዓለም ዓቀፍ መድረኮች ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር መከናወናቸውን ያነሱት የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው፤ ይህም የተሰሩ ስራዎች ውጤት መሆኑን አንስተዋል።

የመዲናዋን ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰቶ መሰራቱን ያነሱት ኮሚሽነር ጌቱ በዚህም በተለይ ወንጀልን ቅድመ መከላከል ላይ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በተሰሩ ስራዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን አስተዋል።

የህዝቡን እርካታ ለማረጋገጥ በተለይ ዘመኑ የወለዳችውን አዳዲስ ቴክኖሎጅዎችን በማበልፅግና ወደተግባር በማስገባት በበጀት ዓመቱ በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን የተናገሩት ኮሚሽነር ጌቱ፤ በዚህም መንጀልን መቀነስ ስለመቻሉ አስተዋል።

በከፍተኛ የልማት ለውጥ ውስጥ ለምትገኘው አዲስ አበባ ዘመናዊ ከተማነቷን የሚመጥን ዘመናዊ የፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ያስፈልጋታል ያሉት ኮሚሽነሩ፣ ይህንን ገቢራዊ የማድረግ ሂደት በቀጣይ በጀት ዓመት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

በራሄል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review