የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ ተቋማት የሰጠው እውቅናና ሽልማት፤ ለቀጣይ ተልዕኮ የሚያነሳሳ፣ ተጨማሪ ጉልበት የሚሆንና አደራን የተሸከመ መሆኑ ተገለፀ።
የአዲስ አበባ ከተማ የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ፣ ምዘናው በመዛኝና ተመዛኞች መካከል ተገቢ የሆነ ተግባቦት የነበረው መሆኑን ጠቅሰው፣ አገልግሎት አሰጣጡን በማቀላጠፍና በማዘመን፣ ብልሹ አሰራርን በመከላከል፣ የህዝብ እርካታን ከመፍጠር አንፃር የተከናወኑ ተግባራት በምዘናው ወቅት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል ብለዋል።
ቢሮ ኃላፊው አክለውም፣ የሀብት ቁጠባን መሰረት ያደረጉ ስራዎች፣ የህዝብ አስተያየትና ጥቆማን መሰረት ያደረገ ድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ የተሰጠበትን አግባብ በተጨማሪ የአገልግሎት አሰጣጡን ምቹ ከማድረግ አኳያ የተከናወኑ ስራዎችን አንስተዋል።
ተቋማት በአዋጅ የተሰጣቸውን ተግባርና ኃላፊነት አልቆ በመፈጸም፣ ለህዝብ የተገባውን ቃል በማረጋገጥ ሰላምን፣ ልማትንና የትውልድ ግንባታን በማስቀደም እንዲሁም ሀብትን በቁጠባ መጠቀም እንደሚገባ አንስተው ተቋማትንም ለሽልማት ማብቃቱን አጽንኦት ሰጥተዋል።
በኮሙኒኬሽን ስራዎች መረጃ በመለዋወጥ፣ ስራ ወስዶ ፈጥኖ ከመመለስ በተጨማሪ ለቀጣይ ተልዕኮ ለበለጠ አፈጻጸም እንዲዘጋጁ ለማሳሰብና በተቋማት መካከል ጤናማ የውድድር መንፈስ ለመፍጠር ያለመ ነው ብለዋል።
በአለኸኝ አዘነ