የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛው ፍርድ ቤት በአለም ዙሪያ የወደፊት የአየር ንብረት ላይ ሙግት ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታውቋል።
በሄግ የሚገኘው የአለም አቀፍ ፍርድ ቤት 15 ዳኞችን የያዘ እና የአማካሪ አስተያየት በመባል የሚታወቀው ፤ ምክክሩ በህግ አስገዳጅነት የሌለው መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
ዳኞቹ የወደፊት የአየር ንብረት ጉዳዮች ችላ ሊባሉ አይገባም ሲሉ ይናገራሉ። ምክክሩ በፍርድ ቤት ታሪክ ውስጥ እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን ባለሙያዎቹ ተናግረዋል።
የሰው ልጅን ሕልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ ጉዳዮችን ለማስወገድ ዓለም አቀፍ ህጎች እና ግዴታዎች በምክክሩ እንደሚብራሩ ታውቋል።
የአለም አቀፉ ፍርድ ቤት ችሎት በታህሳስ ወር ላይ የሁለት ሳምንታት ችሎት ያደረገ ሲሆን ፤ የባህር ከፍታ መጨመር የህልውና ስጋት መሆኑን አሳውቋል።
በአጠቃላይ በነበረው ችሎት የአለምአቀፍ ድርጅቶች ፤ የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ዳኞችን የአየር ንብረት ለውጥን የተመለከቱ ጥያቄዎችን ጠይቀዋል።
የ2015 የፓሪስ ስምምነትን ጨምሮ አሁን ያሉት የአየር ንብረት ስምምነቶች ፤ ለውሳኔው መሰረት ሊሆኑ ይገባል ሲሉ የበለፀጉ ሀገራት ለዳኞቹ አስተያየት መስጠታቸውን ሮይተርስ አስነብቧል።
በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት በበኩላቸው ፤ በአየር ንብረት ለውጥ ለሚመጡ ችግሮች የገንዘብ እርዳታ ለማድረግ ጠንከር ያሉ እርምጃዎች እንዲወስዱ ተከራክረዋል።
በ2015 በፓሪስ በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ከ190 በላይ ሀገራት የአለም ሙቀት መጨመርን ወደ 1.5 ዲግሪ ሴልሺየስ ለመገደብ ጥረቶች ለማድረግ መታቀዱ ይታወቃል ።
በስምምነቱ ላይ የአለም አቀፍ የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀትን እድገት ለመግታት አለመቻሉ ተገልጿል ።
በብርሃኑ ወርቅነህ