አሜሪካ ከጃፓን ጋር የንግድ ስምምነት ማድረጓን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስታውቀዋል።
ከአሜሪካ ዋና የንግድ አጋራት መካከል የምትገኘው ጃፓን ተሽከርካሪን ጨምሮ በሌሎች ሸቀጦች ላይ 25 በመቶ የነበረውን ታሪፍ ወደ 15 በመቶ ዝቅ የሚያደርግ የታሪፍ ቅነሳ ስምምነት ከአሜሪካ ጋር መስማማታቸውን አስታውቃለች።
ዶናልድ ትራምፕ ከጃፓን ጋር የተደረገውን ስምምነት በንግድ ስምምነት ታሪክ ትልቁ መሆኑን ተናግረዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
በስምምነቱ በሗላ አሜሪካ ከጃፓን ኢንቨስትመንት የ550 ቢሊዮን ዶላር ጥቅም እንደምታገኝ ተዘግቧል።
በተጨማሪም ትራምፕ በፊሊፒንስ እና ኢንዶኔዢያ ጋርም ከስምምነት መድረሳቸውን አስታውቀዋል።
በሃገራቱ ሸቀጦች ላይ የተጣለው ታሪፍ ወደ 19 በመቶ ዝቅ መደረጉን እና ኢንዶኔዢያ በአንፃሩ በአሜሪካ ሸቀጦች ላይ ከጣለችው ታሪፍ 99 በመቶ የሚሆነውን እንደምታነሳ በዘገባው ተካቷል።
ነጩ ቤተ-መንግስት ስለስምምነቱ ዝርዝር መረጃ ይፋ አላደረገም።
በሊያት ካሳሁን