ኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የስራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የዛምቢያ አምባሳደር ሮዝ ካሸምቤ ሳካላን እና የቱኒዝያ አምባሳደር አብዱልሃሚድ ግሃሪቢን አሰናበቱ።
ፕሬዚዳንት ታዬ አምባሳደሮቹ በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ሀገራቱ ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ እንዲጎለብት ላደረጉት አስተዋፅኦ አመስግነዋል።
በሌላ በኩል ተሰናባች አምባሳደሮቹ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫነቷን በሚመጥን መልኩ ሁሉን አቀፍ እድገት እያስመዘገበች መሆኗን በቆይታቸው መገንዘባችውን ተናግረዋል።
ፕሬዚዳንት ታዬ ከሁለቱ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር ያደረጉትን ውይይት የተከታተሉት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ዘሪሁን አበበ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ከዛምቢያ እና ቱኒዝያ ጋር ያላት ግንኙነት ዘርፈ ብዙ ነው ማለታቸዉን ተዘግቧል፡፡