ሀሰተኛ የባቡር ትራንስፖርት ትኬት በማዘጋጀት ሲሸጥ የነበረ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ሰራተኛ በቁጥጥር ስር ዋለ

You are currently viewing ሀሰተኛ የባቡር ትራንስፖርት ትኬት በማዘጋጀት ሲሸጥ የነበረ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ሰራተኛ በቁጥጥር ስር ዋለ

AMN ሐምሌ 18 ቀን 2017 ዓ/ም

ሀሰተኛ የባቡር ትራንስፖርት ትኬት በማዘጋጀት ሲሸጥ የነበረ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ሰራተኛ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ያፌት አለማየው የተባለው ተጠርጣሪ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ትኬት ቆራጭ መሆኑን እና የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው ሐምሌ 14 ቀን 2017 ዓ/ም በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው 7ኛ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው የድርጅቱ የቲኬት መሽጫ ቢሮ መሆኑን ፖሊስ አስታዉቋል፡፡

ተጠርጣሪው ከድርጅቱ ህጋዊ ቲኬት ጋር የሚመሳሰል ሀሰተኛ ትኬቶችን በማዘጋጀት ለደንበኞች ሲሸጥ በቲኬት ተቆጣጣሪዎች ጥቆማ ሰጪነት ከ553 ሀሰተኛ ትኬቶች ጋር እጅ ከፍንጅ ተይዞ ምርመራ እየጣራበት መሆኑን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

ግለሰቡ የተጣለበትን ኃላፊነት ወደ ጎን በማለት የመንግስትና የህዝብ ሀብትን በህገ-ወጥ መንገድ ለግል ጥቅሙ ለማዋል በፈፀመው ወንጀል በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review