ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና ጄ. መሃመድ ጋር ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት ኢትዮጵያ ለመጪዎቹ ሶስት ቀናት በአዲስ አበባ የሚከናወነውን ሁለተኛውን የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ በጋራ በማዘጋጀቷ ኩራት ይሰማታል ብለዋል።
ዛሬ ማለዳ የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ዋና ፀሐፊ የሆኑትን አሚና ጄ. መሃመድን በጽሕፈት ቤታችን ተቀብያለሁ።
በመላው አፍሪካ እና በተቀረውም አለም ዘላቂ፣ አካታች እና በተለያዩ ፈተናዎች የማይበገር የምግብ ሥርዓት አስፈላጊነትን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።
ኢትዮጵያ በተቀናጁ ፖሊሲዎቿ፣ ለአየር ንብረት ጥበቃ ምላሽ ሰጪ በሆነ የግብርና ሥራዋ ብሎም በምግብ ዋስትና እና ለሁሉም የተመጣጠነ ምግብ በማቅረብ ማኅበረሰብ መር ዘዴዎቿ የምግብ ሥርዓትን ለማሻሻል ባላት ፅኑ አቋም እና ተግባር ቀጥላለች ሲሉ ገልጸዋል።