ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በዘላቂ የግብርና ልማት እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ፋኦ የኢትዮጵያ ቁልፍ አጋር ሆኖ መቀጠሉን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ” የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ጉባኤ በአዲሰ አበባ በሚጀምርበት እለት የአለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት(ፋኦ) ዋና ዳይሬክተር ኩ ዶንግዩ በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጡ” ብለዋል።
በዘላቂ የግብርና ልማት እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ፋኦ የኢትዮጵያ ቁልፍ አጋር ሆኖ መቀጠሉንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የጠቀሱት።