ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት የአለምአቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ (IFAD) ፕሬዝዳንት አልቫሮ ላሪዮ እንኳን ወደ ኢትዮጵያ በደህና መጡ እላለሁ ብለዋል።
ተቋሙ የገጠሩን ማኅበረሰብ በማብቃት አካታች እና ዘላቂ የግብርና ልማት ለማሳደግ አይነተኛ ሚና መጫወቱን ቀጥሏል።
ለፈተና የማይበገር አኗኗርን ለመገንባት ከተቋሙ ጋር ላለን ጠንካራ ትብብር እና የጋራ ተልዕኮ ከፍ ያለ ዋጋ እንሰጣለን ሲሉ ገልጸዋል።