ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች እና የሀገራት ተወካዮች በምሥራቅ ሸዋ ዞን የቦራ የስንዴ ክላስተር ማሳ ተመለከቱ

You are currently viewing ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች እና የሀገራት ተወካዮች በምሥራቅ ሸዋ ዞን የቦራ የስንዴ ክላስተር ማሳ ተመለከቱ
  • Post category:ልማት

AMN ሃምሌ 20/2017

ለ2ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ አዲስ አበባ የተገኙ ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች እና የሀገራት ተወካዮች በምሥራቅ ሸዋ ዞን የቦራ የስንዴ ክላስተር (ኩታ ገጠም) ማሳ ተመልክተዋል።

ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየሠራችው ያለውን ሂደት እንግዶቹ በአካል እንዲመለከቱ ያስቻለ ምልከታ መሆኑ ተገልጿል።

በአካባቢው የሙዝ ልማት ኩታ ገጠም እርሻም በእንግዶቹ የሚታይ ይሆናል።

በዚህ ጉብኝት የ19 ሀገራት ተወካዮች እና የዓለም አቀፍ ድርጅት ተወካዮች ተካትተዋል።

በምሥራቅ ሸዋ ዞን የቦራ የስንዴ ክላስተር (ኩታ ገጠም) 32 ሺህ ሔክታር መሬት በስንዴ ይለማል።

ለምግብ ሥርዓት ጉባኤ አዲስ አበባ የተገኙት እንግዶች ከምግብ ጋር የተያያዙ የኢትዮጵያን ሥራዎች በተለያዩ ቦታዎች እየጎበኙ ይገኛሉ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review