ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የተባበሩት መንግሥታት ረዳት ዋና ፀሐፊ እና የዩኤንዲፒ የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር አሁና ኢዚያኮንዋንን ተቀበሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት የተባበሩት መንግሥታት ረዳት ዋና ፀሐፊ እና የዩኤንዲፒ የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር አሁና ኢዚያኮንዋ እንኳን በደህና መጡ እላለሁ ብለዋል፡፡
ዩኤንዲፒ በመላው የአፍሪካ አኅጉር አካታች ልማትን ለማሳደግ፣ ለሰላም ግንባታ እና ፅናት ያለውን ጠንካራ ትብብር በእጅጉ እናደንቃለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልጸዋል፡፡