ኢትዮጵያ በፍጥነት እየተለወጠች ነው ሲሉ የዓለም ምግብና እርሻ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዡ ዳዩንግ ተናገሩ

You are currently viewing ኢትዮጵያ በፍጥነት እየተለወጠች ነው ሲሉ የዓለም ምግብና እርሻ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዡ ዳዩንግ ተናገሩ

AMN- ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም

ለተመድ የሥርዓተ ምግብ ጉባኤ አዲስ አበባ የሚገኙት የዓለም ምግብና እርሻ ድርጀት ዳይሬክተር ዡ ዳዩንግ በኢትዮጵየ እየመጣ ያለውን ሁለንተናዊ ለውጥ አስደናቂ ነው ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ የተከናወኑ የተለያዩ ሰው ተኮር የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው የተመለከቱት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ኢትዮጵያ በፈጣን የለውጥ ሂደት ውስጥ ትገኛለች ብለዋል፡፡

በሀገሪቱ አካታች እና ሁሉን አቀፍ ልማት እንድመዘገብ በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እያበረከቱ ላለው ጠንካራ አመራር እና እርአያነት ያለው ተግባርም አድናቆታቸውን ገልፀዋል፡፡

አዲስ አበባን አስመልክተው ሲናገሩም፣ አረንጓዴ፣ ንፁህ እና ብርሀናማ ከተማ ሆናለች ብለዋል፡፡

ከሶስት ዓመት በፊት የነበረችው አዲስ አበባ እንዲህ አልነበረችም ያሉት ዡ ዳዩንግ፣ ይህ በአጭር ጊዜ የመጣ ለውጥ የአንድነት እና የትብብር ውጤት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review