ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ከኩባ ሪፐብሊክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆርጌ ሉዊስ ታፒያ ፎንሴካ ጋር ተወያዩ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ከሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ስርዓት ጉባኤ ጎን ለጎን፣ ከኩባ ሪፐብሊክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆርጌ ሉዊስ ታፒያ ፎንሴካ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ እና ኩባ ለሀምሳ ዓመታት የዘለቀ ጠንካራ የዲፕሎማሲ ግንኙነት አላቸው፡፡ ይህንንም ግንኙነት በተለያዩ የትብብር መስኮች ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለችውን የልማት እንቅስቃሴ አድንቀዋል፡፡ በተለይም ባለፉት ዓመታት የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እየሰራች ያለችው ስራ አበረታች መሆኑን ገልፀውልኛል፡፡ በተጨማሪም የተከበሩ ሆርጌ ሉዊስ በአዲስ አበባ የሚታዩ ለውጦች በዕጅጉ እንዳስደነቃቸው ነግረውኛል፡፡
ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆርጌ ሉዊስ ጋር ባደረግነው ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይት፣ የጋራ ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ እንዲሁም በፖለቲካዊ፣ እና ኢኮኖሚያዊ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ትብብርን ለማጠናከር ተስማምተናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡