የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬም እናሳካዋለን በማለት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ፍቅር እና ሰላምን በሞላበት አሻራችንን ማኖር አጠናክረን ቀጥለናል ብለዋል፡፡
በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል አገራዊ ንቅናቄ በመላዉ አዲስ አበባችን ቀጥሏል።
ችግኝ የምንተክለዉ ለአየር ንብረት ለዉጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት ነው።
በዚሁም መሰረት ጎሮ አከባቢ ከመላው የከተማችን ማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በመሆን እንዲሁም ከአዲስ አበባ ፓሊስ ሰራዊት ፣ከደንብ ማስከበር አባላትና የሰላም ሰራዊት እንዲሁም ከኮልፌ ማህበረሰብ ጋር የአዋሽ ወንዝ ገባር በሆነዉ የአቃቂ ወንዝ ዳርቻ ማህበራዊ መስተጋብርን በሚያጠናክር ፣ ፍቅር እና ሰላምን በሞላበት አሻራችንን ማኖር አጠናክረን ቀጥለናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡