አረንጓዴ ዐሻራ የምግብ ዋስትና እንዲረጋገጥ እና ሌማት እንዲሞላ እያደረገ እንደሆነ ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) አመላከቱ

You are currently viewing አረንጓዴ ዐሻራ የምግብ ዋስትና እንዲረጋገጥ እና ሌማት እንዲሞላ እያደረገ እንደሆነ ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) አመላከቱ

AMN ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም

የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የምግብ ዋስትና እንዲረጋገጥ እና ሌማት እንዲሞላ እያደረገ ነው ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሃሳብ እየተከናወነ ባለው በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብር፣ ዘነበ ወርቅ በሚገኘው የኢቢሲ ትምህርት እና ስልጠና ማዕከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

እንደ አንድ ዜጋ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ተሳታፊ በመሆናቸው ደስተኛ መሆናቸውን የገለጹት ዶክተር ለገሰ ቱሉ፤ በዛሬው ዕለት የቡና ችግኝ መትከላቸውን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን በአንድ ጀምበር የችግኝ መርሐ ግብር ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው፣ ለምግብነት የሚውሉ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚረዱ ብዙ ፋይዳ ያላቸው ችግኞችን በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከሉ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

በኢቢሲ ትምህርት እና ስልጠና ማዕከል ግቢ በተካሄደው የችግኝ ተከላ በመርሐ ግብር፣ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳን ጨምሮ የኢቢሲ ሰራተኞችና አመራሮች የቡና ችግኞችን በመትከል አረንጎዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review