የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዝናብ አጠር በሆኑ አካባቢዎች መከናወኑ የጎላ ሚና እንደሚኖረው አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ

You are currently viewing የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዝናብ አጠር በሆኑ አካባቢዎች መከናወኑ የጎላ ሚና እንደሚኖረው አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ

AMN- ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ በሶማሌ ክልል በአንድ ጀንበር 700 ሚሊዮን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን አስጀምረዋል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዝናብ አጠር በሆኑ አካባቢዎች መከናወኑ የአካባቢ ደህንነትን በማስጠበቅ በኩል የጎላ ሚና እንደሚኖረው አቶ ተመስገን ገልጸዋል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ከምግብ ተጠቃሚነት ጋር በማስተሳሰር በተሰራው ስራ ከፍተኛ ውጤት እንደተገኘበትም ነው አቶ ተመስገን ያነሱት፡፡

መርሃ ግብሩ የምግብ ዋስትናን እንዲያረጋግጥ በተሰራው የማስተሳሰር ስራ በርካታ ለምግብነት የሚያገለግሉ የአትክልት፣ የፍራፍሬ ተክሎች እና የቡና ችግኞች እንዲተከሉ በመደረጉ፣ በመጀመሪያዎቹ አመታት የተተከሉ የቡና ተክሎች አሁን ላይ ምርት መስጠት ጀምረዋል ብለዋል፡፡

የሶማሌ ክልል ብዙውን ጊዜ ዝናብ አጠር በመሆኑ ዛሬ የምንተክላቸወ ችግኞች ለወደፊቱ የተሻለ የአካባቢ ደህንነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸውም አመላክተዋል፡፡

በዛሬው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በክልሉ ከ2.5 ሚሊዮን በላይ ችግኞች እንደሚተከሉ የጠቆሙት አቶ ተመስገን፣ ይህም በክልሉ ለሚደረገው የግብርና ስራ እንቅስቃሴ የላቀ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

የሶማሌ ክልል በርካታ የከርሰ ምድር ፀጋዎች ያሉት ክልል በመሆኑ፣ የተጀመረው የግብርና ስራ የበለጠ እንዲጠናከርም አመላክተዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review