የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) መንግስት ለቀጣዩ ትውልድ ምንዳ ለማውረስ ከጀመራቸው መካከል አረንጓዴ ዐሻራ ዋናው ነው ብለዋል።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሂደዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ መንግስት ለቀጣዩ ትውልድ ምንዳን ለማውረስ የሚተገብራቸው መርሐ ግብሮች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ ነው።
ከመርሐ ግብሮቹ መካከል አንዱና ዋናው አረንጓዴ ዐሻራ መሆኑን ገልጸዋል።
ዜጎች የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ጥቅምን በመገንዘብ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ እንደሆነ በመጥቀስ፤ በዛሬው የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብርም ህብረተሰቡ በከፍተኛ ደረጃ እየተሳተፈ ነው ብለዋል።