ሥነ ምህዳርን ከሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ጋር አስተሳስሮ መሥራት ለማይበገር የኢኮኖሚ እድገት ቁልፍ ነው ሲሉ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ.ር) ተናገሩ

You are currently viewing ሥነ ምህዳርን ከሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ጋር አስተሳስሮ መሥራት ለማይበገር የኢኮኖሚ እድገት ቁልፍ ነው ሲሉ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ.ር) ተናገሩ

AMN- ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ.ር)ን ጨምሮ የሚኒስቴሩ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች በአዲስ አበባ አይ ሲቲ ፓርክ አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።

በዚህ መርሐ ግብር መልእክት ያስተላለፉት ሚኒስትሩ ሀገሪቱን በአረንጓዴ ልማት ለማልበስ እንደዚህ አይነት መነቃቃቶች እና መርሐ ግብሮች ወሳኝ ናቸው ብለዋል።

ሥነ ምህዳርን ከሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ጋር አስተሳስሮ መሥራት ለማይበገር የኢኮኖሚ እድገት ቁልፍ በመኾኑ ሚኒሥቴር መሥሪያ ቤቱም ለዚህ ስኬት በትኩረት ይሠራል ብለዋል።

የሚኒስቴሩ ሠራተኞች በመርሐ ግብሩ በመሳተፍ አሻራቸውን በማሳረፉቸው ደስ መሰኘታቸውንና ተንከባክበው ለማሳደግም ቁርጠኛ ስለመኾናቸውን ተናግረዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review