700 ሚሊየን ችግኞች የሚተከሉት ካርታ በተዘጋጀላቸው ቦታዎች ላይ መሆኑን አደፍርስ ወርቁ (ዶ/ር) ገለጹ

You are currently viewing 700 ሚሊየን ችግኞች የሚተከሉት ካርታ በተዘጋጀላቸው ቦታዎች ላይ መሆኑን አደፍርስ ወርቁ (ዶ/ር) ገለጹ

AMN- ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም

700 ሚሊየን ችግኞች የሚተከሉት ካርታ ተዘጋጅቶላቸው ሊቆጠሩ በሚችሉባቸው ቦታዎች ላይ መሆኑን ብሔራዊ የአረንጓዴ ዐሻራ ቴክኒክ ኮሚቴ አስተባባሪ አደፍርስ ወርቁ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

2 ሚሊዮን ሄክታር የሚያገግም መሬት መዘጋጀቱን ጠቅሰው፣ ከዚህ ውስጥ 668 ሺህ ሄክታር መሬት ካርታ የተዘጋጀለት እንደሆነ ገልጸዋል።

በዚሁ መሰረት የ294 ሺህ ሄክታር ስፋት ባላቸው 13 ሺህ 84 ቦታዎች ላይ ችግኞቹ እየተተከሉ እንደሆነም ጠቁመዋል።

ከካርታ ውጭ ባሉ ቦታዎች የሚተከሉ ችግኞች በመኖራቸው ቁጥሩ ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል አስተባባሪው ጠቁመዋል።

ለዘንድሮ የአንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በ116 ሺህ ችግኝ ጣቢያዎች 3.5 ቢሊየን የደን እና 4 ቢሊየን የጥምር ደን ችግኞች መዘጋጀታቸውንም ጠቁመዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሀገር በቀል ዛፎችን የመትከል ባህሉ እየተስፋፋ እንደሚገኝም ዶክተር አደፍርስ ተናግረዋል።

በአንድ ጀምበር 700 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብር ኢትዮጵያጵያውያን ሕብረታቸውን የሚያፀኑበት መልካም አጋጣሚ እንደሆነም አስተባባሪው ተናግረዋ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review