የሰው ልጅ ህይወት ከተፈጥሮ ጋር ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማስተሳሰር በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር መሳተፍ የዜጎች ግዴታ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ፡፡
ኢትዮጵያ ለልጆቻችን እና ለልጅ ልጆቻችን የተመቸች ሀገረ እንድትሆን፣ አሁን ላይ በሀላፊነት መስራት እንደሚገባም ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል።
ለሚመጣው ትውልድ ትምህርትን ብቻ ሳይሆን የተመቸች ዓለምን ማውረስ ይገባል ያሉት ሚኒስትሩ፣ ይህንን ሀላፊነት ለመወጣት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ መሳተፍ የሁሉም ዜጎች ሀላፊነት ሊሆን እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የምናከናውነው ተግባር ፖለቲካ አይደለም ያሉት ሚኒሰትሩ፣ በእውቀት ላይ የተመሰረተ የሰው ልጅ ህይወት ከተፈጥሮ ጋር ያለውን ግንኙነት የበለጠ ማስተሳሰር አስፈላጊ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡