የስኬት ባንክ አመራሮች እና ሰራተኞች ‘በመትከል ማንሰራራት’ በሚል መሪ ሃሳብ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ባለው የአረንጓዴ አሻራ ላይ የተለያዩ ሀገር በቀል ችግኞችን በእንጦጦ ፓርክ በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳምጠው አለማየሁ ባስተላለፉት መልዕክት ስኬት ባንክ ባለፉት ዓመታት በሀገራችን የልማትና የምጣኔ ሀብት ዕድገት ውስጥ አሻራቸውን ካስቀመጡ የፋይናንስ ተቋማት መካከል አንዱ ከመሆኑም በተጨማሪ ለሀገሪቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም ትልቅ ተሳትፎ በማድረግ የማህበራዊ ኃላፊነቱን ሲወጣ የቆየ እና አሁንም እየተወጣ ያለ የፋይናንስ ተቋም መሆኑን ገልፀዋል ባንኩ ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል በላከው መረጃ ጠቅሷል፡፡