አርብ እለት በተደረገው ዉይይት የአፍሪካ መሪዎች ፤ በምስራቅ ኮንጎ ለተፈጠረው ግጭት አፍሪካ መር የሰላም እና የመፍትሔ ባለቤት መሆን እንዳለባቸው በዉይይቱ ተገልጿል ሲል አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል።
ውይይቱን የመሩት የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እና የዚምባብዌው ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ፤ የምስራቅ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ግጭትን ወደ ሰላም የሚያመጣ አፍሪካ መር የሰላም እና የመፍትሔ ባለቤት መኖር እንዳለበት መወሰናቸው ታውቋል።
የኬንያው ዊሊያም ሩቶ እና የዚምባብዌው ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ፤ ከአፍሪካ ህብረት እና አባል ሀገራት ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት ፤ በኮንጎ ሰላም ለማምጣት በአፍሪካ ህብረት አዲስ አበባ የሚመራ የተቀናጀ የሰላም እና የመፍትሔ ባለቤት እንዲኖር ለማድረግ ውሳኔዎችን አስተላልፈዋል።
በሐምሌ ወር በኮንጎ እና በሩዋንዳ ኤም 23 በሚደገፉት አማፂያን መካከል ፤ በምስራቅ ኮንጎ የተኩስ አቁም ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን በጎሳዎች ውጥረት እና የበለፀጉ ማዕድናትን ፍለጋ በሚደረገው ሂደት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መገደላቸውም ተገልጿል።
ይህም በአፍሪካ ረጅም ጊዜ ከወሰዱ ግጭቶች መካከል አንዱ ያደርገዋል ሲል አፍሪካ ኒውስ ዘግቦታል።
የአፍሪካ ህብረት በኳታር የተመቻቸውን የሰላም ጥረትም ትልቅ ምዕራፍ ነው ብሎታል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በሩዋንዳ እና በኮንጎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች መካከል የተደረገውን የሰላም ስምምነት ከ30 ዓመታት ጦርነት በኋላ የተደረገ ጠቃሚ የስምምነት ጊዜ ነው ሲል ጠርቶታል።
ኤም 23 በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ባደረገው ጦርነት ፤ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሞት እና ሰባት ሚሊዮን ዜጎች እንዲፈናቀሉ ማድረጉም ታውቋል።
በብርሃኑ ወርቅነህ