የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገጽታ የቀየረ የፈጠራ እና የፍጥነት ውጤት ማሣያ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ ገለጹ

You are currently viewing የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገጽታ የቀየረ የፈጠራ እና የፍጥነት ውጤት ማሣያ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ ገለጹ
  • Post category:ልማት

AMN ሐምሌ 27/2017

የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገጽታ የቀየረ የፈጠራ እና የፍጥነት ውጤት ማሣያ መሆኑን የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ ገለጹ፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት አባላት ከእንጦጦ እስከ አራት ኪሎ ፕላዛ፣ የሳይንስ ሙዚየም ቋሚ ኤግዚቪሽንና መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ጎብኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ከብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት አባላት ጋር በመሆን አዲሱን እና ከእንጦጦ እስከ አራት ኪሎ ፕላዛ ተሠርቶ የተጠናቀቀውን ኮሪደር ዛሬ ጠዋት ተመልክተናል ብለዋል።

ይኽ አስደናቂ ለውጥ ከተካሄደባቸው የከተማችን ክፍሎች አንዱ ነው በማለትም ገልጸዋል።

በጉብኝቱ ላይ የተሳተፉት የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ እንደተናገሩት፤ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገጽታ የቀየረ ነው፡፡

የሳይንስ ሙዚየም ቋሚ ኤግዚብሽን የኢትዮጵያን መጻኢ ተስፋ የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመው፤ ኢትዮጵያ ወደ ዘላቂ ልማት ለምታደርገው የለውጥ ጉዞ ታላቅ ምዕራፍ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የተመለከቷቸው የልማት ፕሮጀክቶች የፍጥነትና የፈጠራ ውጤቶች መሆናቸውን ጠቁመው፤ ከሥራ ፈጠራ እና ከሌሎችም አኳያ የህዝቡን ኑሮ የቀየሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

በሀገር ደረጃ ተግባራዊ የተደረጉ ሁሉም ኢኒሼቲቮች በሶማሌ ክልል መጀመራቸውን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ የጅግጅጋ ከተማ የኮሪደር ልማት ስራዎች በቅርቡ እንደሚመረቁ መግለጻቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በክልሉ የማደራጃት ስራዎች መጀመራቸውን ጠቁመው፤ የገጠር ኮሪደር፣ የሌማት ትሩፋት እንዲሁም በአረንጓዴ ዐሻራ ውጤታማ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከእንጦጦ እስከ አራት ኪሎ ፕላዛ በአስደናቂ ሁኔታ የተገነባው የኮሪደር ልማት የእግረኛና ብስክሌት መንገዶች፣ የመንገድ ዳር መብራቶች፣ በሽሮ ሜዳ የተገነቡ ዘመናዊ ሱቆችን ያካተተ ነው።

የኮሪደር ልማት ሥራው የሕፃናት መጫወቻዎች፣ ሰፋፊ የእግር ኳስ ሜዳዎች ለሕዝብ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግንባታዎች ተካተውበታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review