ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በዓለም የንግድ ድርጅት(ጄኔቫ) የአፍሪካ ህብረት ቋሚ መልዕክተኛ ሆነው መሾማቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ለዚህ ቁልፍ ቦታ መምረጣቸውን ኢትዮጵያ እንደምታደንቅ ያስታወቀው ሚኒስቴሩ ይህም ህብረቱ ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ አፍሪካን በመወከል እየተወጣች ላለው ሚና የሰጠውን ትልቅ ዋጋ የሚያሳይ ነው ብሏል።
ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ባላቸው የካበተ የአመራርነት ልምድ የተሰጣቸውን አዲስ ኃላፊነት በብቃት እንደሚወጡ ሙሉ እምነቱ መሆኑንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) የኢፌዴሪ ግብርና ሚኒስትርነትን ጨምሮ በተለያዩ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ መስራታቸውን በመግለጫው ተጠቅሷል።