ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሴቶችን ወደ ኃላፊነት እንዲመጡ በማድረግ እና የሴቶች ውሳኔ ሰጪነት ሚና እንዲጎለብት በማድረጋቸው፣ የኢትዮጵያ ሴቶች የእውቅና ሽልማት አበርክተውላቸዋል፡፡
በሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ በሚገኘው የሴት አመራሮች መድረክ ላይ በተደረገ የእውቅና መርሀግብር፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የይቻላል መንፈስ በሴቶች ዘንድ እንዲጎለብትና ውጤታማም እንዲሆኑ የተጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑን በመድረኩ ተገልጿል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሴት አመራሮችን በማብቃት፣ ወደፊት እንዲመጡ እና ሁለንተናዊ ድጋፍ በማድረግ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ “የኢትዮጵያ ሴቶች ያመሰግኑሃል” የሚል የምስጋና የእውቅና ሽልማት አበርክተዋል።
ሽልማቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩን በመወከል በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ተቀብለዋል።
የለውጡ ትሩፋት የሆኑ ሴት አመራሮች መድረክ “ሴት አመራሮች ለኢትዮጵያ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ በሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ ነው።
በሄለን ጀምበሬ