የአፍሪካ ሀገራት ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር በአዲሱ ታሪፍ ዙሪያ ዳግም ሊደራደሩ ነው

You are currently viewing የአፍሪካ ሀገራት ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር በአዲሱ ታሪፍ ዙሪያ ዳግም ሊደራደሩ ነው

AMN- ነሐሴ 4/2017 ዓ.ም

የፕሬዚዳንት ትራምፕ አዲሱ ታሪፍ ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በብዙ የአፍሪካ ሀገራት ላይ ተግባራዊ ሆኗል።

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ፣ አንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ የስራ እጦት ያለባቸው መሆኑን ገልፀው፣ አሁንም በአዲሱ የትራምኘ ታሪፍ ዙሪያ እንደገና ለመደራደር እንደሚፈልጉ በመግለፅ ከትራምፕ ጋር መነጋገራቸው ታውቋል።

እንደ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጽህፈት ቤት ከሆነ ራማፎሳ እና ትራምፕ ከደቡብ አፍሪካ ወደ አሜሪካ በሚላኩ ምርቶች ላይ የ30 በመቶ አዲሱ ታሪፍ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ረቡዕ ዕለት መነጋገራቸውን አስታውቀዋል።

ሁለቱ መሪዎች ተጨማሪ ውይይቶችን ለማድረግ መወሰናቸውንም አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል።

ምንም እንኳ ትራምኘ ደቡብ አፍሪካን ቢነቅፉም ደቡብ አፍሪካ ግን አሁንም ከአሜሪካ ጋር በድርድር ነገሮች እንደሚፈቱ እንደምታምን አስታውቃለች።

የደቡብ አፍሪካ ጎረቤቶች የሆኑት ቦትስዋና እና ሌሴቶ፣ አሁንም የታሪፍ መጠን በሚሻሻልበት ሁኔታ ዙሪያ ለመደራደር ተስፋ ማድረጋቸው ተገልጿል።

በብርሃኑ ወርቅነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review