ሰው ተኮር የልማት ስራና የበጎነት ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ

You are currently viewing ሰው ተኮር የልማት ስራና የበጎነት ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ
  • Post category:ልማት

AMN – ነሐሴ 5/2017 ዓ.ም

‎የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ምስክር ነጋሽ (ዶ/ር) ከአማኑኤል ቤተክርስቲያን ሃለዎት አጥቢያ ጋር በመተባበር የአምስት አቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ መርሃ ግብር በወረዳ 3 መጀመሩን ተናግረዋል።

‎በመንግስት እየተተገበረ ያለው ሰው ተኮር ልማትና በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚደረገው የበጎ አድራጎት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የተናገሩት ዋና ስራ አስፈጻሚው፣ የአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስን ጨምሮ ለሚካሄዱት የበጎ አድራጎት ሰራዎች ባለሃብቶችና ምግባረ ሰናይ ድርጅቶች ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

‎የአማኑኤል ቤተክርስቲያን የሃለዎት አጥቢያ ቤተክርስቲያን ስራ አስኪያጅ ተክሌ ገብረእግዚአብሔር፣ ተቋማቸው በበጎ አድራጎት ተግባራት ውስጥ በስፋት እየተሳተፈ መሆኑን ጠቅሰው፣ በወረዳ 3 የተጀመረው የአቅመ ደካሞች የቤት እድሳት መርሃ ግብር በአጭር ጊዜ አጠናቀው እንደሚያስረክቡ ቃል ገብተዋል።

‎ከአጼ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግስት ጀምሮ አካባቢው ላይ መኖራቸውን የሚናገሩት የቤታቸው ዕድሳት የተጀመረላቸው አቅመ ደካሞች፣ የክፍለ ከተማውን አስተዳደርና በየደረጃው ያሉ አካላት ላደረጉላቸው ድጋፍና የበጎነት ተግባር ምስጋና አቅርበዋል።

‎በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የተጀመረው የአምስት አቅመ ደካሞች የቤት እድሳት ስራ ወጪው 5.6 ሚሊዮን ብር እንደሚገመት ተጠቅሷል።

በምትኩ ተሾመ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review