የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያው አቻቸዉ ቭላድሚር ፑቲን በመጪዉ አርብ በአላስካ በሚኖራቸዉ ቆይታ የተወሰኑ ግዛቶችን ለዩክሬን ለማስመለስ እንደሚሞክሩ ተናግረዋል፡፡
ሩሲያ ዋና ዋና የሚባሉትን ጨምሮ የዩክሬንን ሰፊ ግዛት ተቆጣጥራለች፡፡ በዉይይታችን የተወሰነውን ግዛት ወደ ዩክሬን ለመመለስ እንሞክራለን ሲሉ ዶናልድ ትራምፕ ተደምጠዋል፡፡
በአላስካ የሚካሄደዉ ዉይይት ቭላድሚር ፒቲን ጦርነቱን እንዲያቆም የሚያሳስብ የደስታ ስብሰባ ነዉ ሲሉ የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ ሁለቱ ሃገራት የተወሰኑ ግዛቶችን ሊለዋወጡ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡
በዚህ ዉይይት ሩሲያ ምን መሬት ለዩክሬን ልትሰጥ እንደምትችል የታወቀ ነገር ባይኖርም መሬት መለዋወጥ የሚለውን ሃሳብ ሲነሳ ይህ የመጀመሪያ እንዳልሆነ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ኪየቭ እስካሁን ድረስ የትኛውም የሩሲያ ግዛት ይገባኛል የሚል ጥያቄ አቅርባ አታዉቅም፡፡
ቀጣዪ ውይይት የሁለቱን ሃገራት መሪዎች ያሳተፈ ሊሆን እንደሚችልም ተነግሯል፡፡
በሌላ በኩል የአላስካውን ቀጠሮ ዜና ተከትሎ ኬቭን ያላሳተፈ ማንኛውም አይነት ድርድር ውጤት እንደማይኖረው ዘለንስኪ አመላክተዋል።
በሊያት ካሳሁን