የኢትዮጵያን የወደፊት ዲፕሎማሲ የሚመሩ ወጣቶችን ለማፍራት ወደ ተግባር መገባቱ ተገለፀ

You are currently viewing የኢትዮጵያን የወደፊት ዲፕሎማሲ የሚመሩ ወጣቶችን ለማፍራት ወደ ተግባር መገባቱ ተገለፀ

AMN – ነሐሴ 6/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያን የወደፊት ዲፕሎማሲ የሚመሩ ወጣቶችን ለማፍራት ወደ ተግባር መገባቱን የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ ገለጹ፡፡

የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የተማሪዎች የክረምት በጎ ፈቃድ የዲፕሎማሲና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስልጠና ዛሬ አስጀምሯል፡፡

በክረምት በጎ ፈቃድ የዲፕሎማሲና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስልጠና ጥብቅ በሆነ መስፈርት ተመዝነው ያለፉ ተማሪዎች የሚሳተፉበት መሆኑም ተገልጿል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ፤ ኢንስቲትዩቱ በውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዙሪያ ምርምርና ስልጠና ይሰጣል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ ፋንታ በወጣቶች ላይ የተመሰረተ መሆኑን ገልጸው፤ ኢትዮጵያ የምትከተለው የዲፕሎማሲና ዓለም አቀፍ ግንኙነት የወጣቶችን ንቁ ተሳትፎ ይጠይቃል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የወጣቱ ትውልድ ድምጽ ችላ የሚባልበት ዘመን አልፏል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የክረምት በጎ ፈቃድ የዲፕሎማሲ ስልጠና የወጣቶች ተሳትፎ ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወጣቶች በስልጠናው የድርድር፣ የተግባቦት እና የንግግር ክህሎታችውን በማሳደግና የፈጠራ አቅማቸውን በመጨመር መሰረታዊ ዕውቀት ይጨብጣሉ ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለማሳካት የተለመችውን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ለማሳካት ከመደበኛው ዲፕሎማሲ ባሻገር የወጣቶችን ንቁ ተሳትፎ እንደሚጠይቅም ተናግረዋል፡፡

ስልጠናው የኢትዮጵያን የወደፊት ዲፕሎማሲ የሚመሩና የሚቀርጹ ወጣቶችን ለማፍራት እንደሚያግዝ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲፕሎማቶች የተሰጥኦ ማዕከል መፍጠር ያስችላል ብለዋል፡፡

ወጣቶች በኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ እድገትና ዓለም አቀፍ ተሳትፎ የጎላ አበርክቶ እንዲኖራቸው ያስችላልም ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review