በቴክሳስ የተገኘችው የ14 ዓመት አዛዉንቷ ዶሮ በዕድሜ ትልቋ በመባል በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ሰፍራለች።
ፕርል የተሰኘችው ዶሮዋ በፈረንጆቹ መጋቢት ወር 2011 ላይ መፈልፈሏን የዶሮዋ ባለቤት ሶኒያ ሁል ተናግራለች።
የዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ በተያዘው የፈረንጆቹ 2025 ግንቦት ወር ላይ ዶሮዋ የዓለማችን የዕድሜ ባለፀጋ መሆኗን አረጋግጫለሁ ብሏል።
እንቁላል ጣይ ዶሮዎች ከ6 እስከ 8 ዓመት ድረስ በህይወት የሚቆዩ ሲሆን ፕርል ግን የዚህን ዕጥፍ በምድር ላይ መቆየቷ ለየት አድርጓታል።
ዕድሜዋ እየገፋ በመምጣቱ ምክንያት የእንቁላል ምርቷ መቀነሱን እና እንቅስቃሴዋም መገደቡን የዶሮዋ ባለቤት ሁል ገልፃለች።
የአዛውንቷ ዶሮ ዕድሜ 14 ዓመት ከ69 ቀን ሲሆን በዚህም ዓለም የዶሮ ዕድሜ ክብረወሰን መጨበጥ
ችላለች።
ቀደም ሲል በፈረጆቹ 2023 ላይ በ21 ዓመቷ የሞተችው ፔኔት የተሰኘች ዶሮ ነበረች በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ስሟን ማስፈር የቻለችው ሲል ዩፒ አይ አስነብቧል።
በማሬ ቃጦ