በመላው ደቡባዊ አውሮፓ ከፍተኛ የሙቀት መጠን መጨመርን ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች ሰደድ እሳት መቀስቀሱ ተገለጸ

You are currently viewing በመላው ደቡባዊ አውሮፓ ከፍተኛ የሙቀት መጠን መጨመርን ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች ሰደድ እሳት መቀስቀሱ ተገለጸ

AMN- ነሐሴ 7/2017 ዓ.ም

በደቡባዊ አውሮፓ አንዳንድ አካባቢዎች ለሰደድ እሳት መቀስቀስ እና በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ከመኖሪያ ቤታቸው ለመፈናቀል ምክንያት በሆነው ከፍተኛ ሙቀት፣ በትንሹ የሦስት ሰዎች ህይወት ማለፉም ተገልጿል።

በጣልያን፣ በፈረንሳይ፣ በስፔይን፣ በፖርቹጋል እና በባልካን ሀገራት የተለያዩ አካባቢዎች፣ የእሳት አደጋ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

የሙቀቱ መጠን ከ40 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ እየጨመረ በመሆኑም፣ ከባድ የጤና ጠንቅ እንዳያስከትል ሰዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉም ማስጠንቀቂያዎች እየተሰጡ ነው።

ኤሜት የተባለው የስፔን ሚቲዮሮሎጂ ወኪል በሴቪልና በኮርዶባ የሙቀት መጠን ወደ 44 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ሊደርስ እንደሚችል ሪፖርት አድርጓል።

በስፔን፣ ማድሪድ አቅራቢያ በምትገኘው ትሬስ ካንቶስ፣ በአንድ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ውስጥ የሚሰራ ሰራተኛ በደረሰበት ከባድ የእሳት ቃጠሎ ህይወቱ ማለፉ ተነግሯል።

በሰዓት ከ70 ኪሎ ሜትር በላይ እየነፈሰ የሚገኘው ነፋስ፣ የተቀሰቀሰውን እሳት ወደ መኖሪያ አካባቢዎች እየተጠጋ መሆኑን ተከትሎ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አካባቢውን ለቀው እንዲሸሹ አድርጓል።

የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ፣ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እሳቱን ለማጥፋት ያለ እረፍት እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከባድ የደን ቃጠሎ አደጋ ስለተደቀነብን ጥንቃቄ አድርጉ ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኤክስ ገፃቸው የጥንቃቄ መልዕክት አስፍረዋል፡፡

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review