በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ለሚፈጠሩ የደህንነት ስጋቶችና አደጋዎች አንዱ መንስኤ በቂ የግንባታ የደህንነት ባለሙያ ባለመኖሩ በመሆኑ፣ ይህንን ችግር ለመቅረፍ በአዲስ አበባ በግንባታ ሳይቶች ላይ የደህንነት ባለሙያ እንዲኖር እንደሚደረግ ተጠቁሟል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ከአጋር አካላት ጋር በመሆን ለ3 ቀናት የሚቆይ የግንባታ ደህንነት ስልጠና መሰጠት ጀምሯል።
በስልጠና ማስጀመሪያው የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፣ አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ፣ ለደህንነት የተመረጠችና ዘመናዊ ከተማ የምናደርጋት የኮንስትራክሽን ዘርፍን ይዘን ነው ብለዋል።
በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚሰማራ ዜጋ ሁሉ፣ ከአደጋ የፀዳ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የስራ ቦታ እንዲኖረው ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገልፀዋል።
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ለሚፈጠሩ የደህንነት ስጋቶችና አደጋዎች አንዱ መንስኤ በቂ የግንባታ የደህንነት ባለሙያ ባለመኖሩ እንደሆነ ተገልጿል።
ይህንን ችግር ለመቅረፍ በቀጣይ በአዲስ አበባ በግንባታ ሳይቶች ላይ የደህንነት ባለሙያ እንዲኖር እንደሚደረግ ተጠቁሟል።
በተያዘው በጀት ዓመት ግንባታ ላይ የሚሰሩ 2 ሺህ ዜጎችን ስልጠና ለመስጠት መታቀዱ ተገልጿል።
ሰልጣኞች በበኩላቸው፣ የስራ ላይ ደህንነትን ለማስጠበቅ ያለመ ስልጠና መሰጠቱ የሰራተኞችን ደህንነት ከመጠበቁ ባሻገር ከተማዋ ያለመችውን የግንባታ ጥራት ማስጠበቅ ይችላል ብለዋል።
በንጉሱ በቃሉ