ኢትዮጵያ 2ኛውን የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ እና የአፍሪካ – ካሪቢያን ማህበረሰብ ሀገራት የመሪዎች ጉባኤን ለማስተናገድ ተዘጋጅታለች

You are currently viewing ኢትዮጵያ 2ኛውን የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ እና የአፍሪካ – ካሪቢያን ማህበረሰብ ሀገራት የመሪዎች ጉባኤን ለማስተናገድ ተዘጋጅታለች

AMN- ነሐሴ 7/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ 2ኛውን የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ እና የአፍሪካ – ካሪቢያን ማህበረሰብ ሀገራት የመሪዎች ጉባኤን በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ መዘጋጀቷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ ገለጹ፡፡

2ኛውን የአፍሪካ አየር ንብረት እንዲሁም የአፍሪካ – ካሪቢያን ማህበረሰብ ሀገራት የመሪዎች ጉባኤን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ ከተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተውጣጣው ብሔራዊ ኮሚቴ አባላት እየተደረገ ስላላው ቅድመ ዝግጅት በተመለከተ ውይይት አካሂደዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ እና የብሄራዊ ኮሚቴው ሰብሳቢ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ፣ ጉባዔዎቹን ስኬታማ ሆነው እንዲካሄዱ በማድረግ የኢትዮጵያን የዝግጅት አቅም ከፍታ በማሳየትና በዓለማቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ የሀገራችንን አዎንታዊ ገፅታ ለመፍጠር ግብ ተቀምጦ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በሁነቶቹ ላይ የሀገራት መሪዎች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች የሚገኙበት በመሆኑ፣ ኢትዮጵያን ይበልጥ ለማስተዋወቅ ጥራትና ቅልጥፍና የተጠበቀ የላቀ አገልግሎት ለመስጠት የተሟላ ቅንጅት እየተደረገ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል።

የዝግጅቱ ብሔራዊ ኮሚቴ አባላት ከተለያዩ የፌዴራል ተቋማት እና ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የተውጣጡ ሲሆኑ፣ በየዘርፋቸው ዕቅድ በማውጣት ጉባኤውን የተሳካ ለማድረግ በሎጀስቲክና በጸጥታ ዙሪያ እየሰሩ እንደሚገኙ መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review