ፕሬዚዳንት ዜለንስኪ ከአውሮፓ መሪዎች ጋር ለመምከር በርሊን ገቡ

You are currently viewing ፕሬዚዳንት ዜለንስኪ ከአውሮፓ መሪዎች ጋር ለመምከር በርሊን ገቡ

AMN- ነሐሴ 7/2017 ዓ.ም

የአውሮፓ መሪዎችን ጥሪ ተከትሎ የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ በዛሬው እለት በርሊን ከተማ ገብተዋል፡፡

በቀጣዩ አርብ ከሚካሄደው የአሜሪካ- ሩሲያ ጉባኤ አስቅድሞ ነው ዜለንስኪ ወደ በርሊን ያቀኑት፡፡

የእንግሊዙን ጠቅላይ ሚኒስተር ኬር ስታርመርን ጨምሮ ሌሎች የአውሮፓ መሪዎች ፕሬዚዳንት ትራምፕ እና ቭላድሚር ፑቲን አርብ እለት በሚካሄደው ጉባኤ ላይ ዩክሬንን ያገለለ ውሳኔ ላይ ሊደርሱ እንደማይገባ አቋም ይዘዋል፡፡

ከጉባኤው አስቀድሞ በርሊን የደረሱት የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ዜለንስኪ፣ ወደ በርሊን ከመብረራቸው በፊት ለሰላም ሲባል ሩሲያ ላይ ጫና ማሳደር እንደሚገባ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

ለሁለቱ ሀገራት ጥቅም ሊሰጥ የሚችል የሠጥቶ መቀበል አካሄድ ሊኖር እንደሚችል ፕሬዚዳንት ትራምፕ ባለፈው ሳምንት ገልጸው ነበር፡፡

እንደ ቢቢሲ ዘገባ በአሁኑ ወቅት 20 በመቶ የሚሆነው የዩክሬን ግዛት በሩሲያ ቁጥጥር ሥር ነው የሚገኘው፡፡

የአውሮፓ መሪዎች እና ፕሬዚዳንት ዜለንስኪ፣ የዩክሬን ጥቅም በሚከበርበት ሁኔታ ላይ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የቪዲዮ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በማሬ ቃጦ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review