የቼልሲ ተጫዋቾች ከዓለም የክለቦች ዋንጫ ውድድር ያገኙትን ቦነስ ግማሹን ለዲያጎ ጆታ ቤተሰቦች ሊሰጡ ነው

You are currently viewing የቼልሲ ተጫዋቾች ከዓለም የክለቦች ዋንጫ ውድድር ያገኙትን ቦነስ ግማሹን ለዲያጎ ጆታ ቤተሰቦች ሊሰጡ ነው

AMN – ነሃሴ 08/2017 ዓ.ም

ቼልሲ ለዲያጎ ጆታ እና ወንድሙ አንድሬ ቤተሰቦች የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ወስኗል ፡፡

ዘ አትሌቲክ እንደዘገበው ከሆነ የቼልሲ የቡድን አባላት በዓለም የክለቦች ዋንጫ ያገኙትን ጉርሻ ግማሹን ለጆታ ቤተሰቦች ለመስጠት ወስነዋል ፡፡

ፓሪሰን ዠርማን 3ለ0 አሸንፎ የዓለም የክለቦች ዋንጫ ባለቤት የሆነው ቼልሲ ከውድድሩ 114.6 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር እንዳገኘ ተነግሯል ፡፡

ክለቡ ከውድድሩ ካገኘው ገቢ 15.5 ሚሊየን ዶላሩን ለተጫዋቾቹ ለማከፋፈል መወሰኑ ተነግሯል ፡፡

ለጆታ ቤተሰቦችም ተመሳሳይ የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ክለቡ እና ተጫዋቾቹ ተስማምተዋል ፡፡

ዲያጎ ጆታ እና ወንድሙ አንድሬ ሀምሌ 3/2025 በስፔን በደረሰባቸው የመኪና አደጋ ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል ፡፡

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review