በሀገራዊ ምክክሩ የወጣቶች የነቃ ተሳትፎ፣ ትብብርና እገዛ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገለጸ።
”የወጣቶች ሚና እና ተሳትፎ ለውጤታማ ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሃሳብ በባህር ዳር ከተማ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ብሌን ገ/መድህን፤ በሀገሪቱ የሚስተዋሉ የቆዩ ችግሮችን በምክክር በዘላቂነት መፍታት የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ከዝግጅት ምዕራፍ እስከ አጀንዳ ልየታ የምክክር ምዕራፍ ስኬታማ ተግባራትን ማከናወኑን ጠቅሰው በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በዚህ ሂደት የሁሉም ህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎና እገዛ ወሳኝ መሆኑን አንስተው በተለይም የወጣቶች ተሳትፎ የማይተካ ሚና አለው ብለዋል።
በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሀይማኖት አባቶችን፣ የሀገር ሽማግሌዎችን፣ ምሁራን፣ ወጣቶች፣ ሴቶችና ሌሎችን በማሳተፍ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሰራ መሰራቱን አስታውሰዋል።
በመሆኑም በሀገራዊ ምክክሩ የወጣቶች የነቃ ተሳትፎ፣ ትብብርና እገዛ ተጠናከሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በመድረኩ የኮሚሽኑ አመራሮች፣ ወጣቶችና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።