በሀገር አቀፍ ደረጃ ከወረዳ እስከ ፌደራል የመጅሊስ ምርጫ በኡለማዎች ዘርፍ የድምፅ መስጠት ስነ ስርአት በዛሬው እለት ከጁምአ ሶላት በኋላ ይካሄዳል።
በአምስት የተለያዩ ዘርፎች የሚካሄደው የመጅሊስ ምርጫ ከዛሬ ጀምሮ እስከ እሁድ ድረስ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከወረዳ እስከ ፌደራል በየመስጅዶች ምርጫ የሚካሄድ መሆኑ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከወረዳ እስከ ፌደራል ለሚካሄደው የመጅሊስ ምርጫ በዛሬው እለት ከጁምአ ሶላት በኋላ የድምፅ አሰጣጥ ስነ ስርአት እንደሚካሄድ ኢዜአ ዘግቧል።
ለዚህ ምርጫ ህዝበ ሙስሊሙ የምርጫ ካርድ በመያዝ ምእመኑን የሚያገለግሉ አመራሮችን ለመምረጥ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ በተለያዩ ክልሎች የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤቶች የምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ ሃላፊዎች ጥሪ አቅርበዋል።
በአምስት የተለያዩ ዘርፎች የሚካሄደው የመጅሊስ ምርጫ ከዛሬ ነሐሴ 9 እስከ 11 ቀን 2017 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ከወረዳ እስከ ፌደራል በየመስጅዶች የሚካሄድ መሆኑ ይታወቃል።