ሀገርን ጠብቆ ለትውልድ ለማሸጋገር የፖለቲካ ስብራቶችን በሀገራዊ ውይይት መፍታት እንደሚገባ ተገለጸ

You are currently viewing ሀገርን ጠብቆ ለትውልድ ለማሸጋገር የፖለቲካ ስብራቶችን በሀገራዊ ውይይት መፍታት እንደሚገባ ተገለጸ

AMN- ነሐሴ 9/2017 ዓ/ም

ህዝቦቿ በመስዋዕትነት ያቆዩዋትን ሀገር ጠብቆ ለትውልድ ለማሸጋገር የፖለቲካ ስብራቶችን በሀገራዊ ውይይት መፍታት እንደሚገባ ተገለጸ።

በኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተዘጋጀው 44ኛ ጉሚ በለል፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ስብራቶች ከትናንት እስከ ዛሬ በሚል ርዕስ የምሁራን ውይይት በክልሉ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ተካሂዷል።

በመርሐ-ግብሩ በቀረበ ጥናትም፣ የፖለቲካ ስብራት መንስኤዎች የታሪክ መዘባትና ሀሰት የሚፈበርኩ የዲጂታል ሚዲያ ቴክኖሎጂዎች እየተበራከቱ መምጣታቸው ዋንኞቹ መሆናቸውን የመወያያ ጥናታዊ ጽሁፉን ያቀረቡት ብርሃኑ ሌንጅሶ (ዶ/ር) አብራርተዋል።

መፍትሄውም የፖለቲካ አለመግባባቶችን ተቀራርቦ በውይይት መፍታት እና የኢትዮጵያን ታሪክ የብዙሃን ህዝቦች መኖሪያ መሆኗን በአግባቡ መገንዘብ እንደሚያስፈልግ እና የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም በውይይቱ ተነስቷል።

በአለሙ ኢላላ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review