ሀገር አቀፍ የዑለማዎች ምርጫ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው

You are currently viewing ሀገር አቀፍ የዑለማዎች ምርጫ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው

AMN – ነሐሴ 9/2017 ዓ.ም

ሀገር አቀፍ ደረጃ የመጅሊስ ምርጫ ዛሬ በዑለማዎች ዘርፍ ምርጫ በአዲስ አበባና ሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች መካሄድ ጀምሯል።

በዚሁ መሰረት የዑለማዎች ዘርፍ ምርጫ በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የወሎ ሰፈር አቡ-ሑረይራ መስጅድና ኢስላማዊ ማዕከልም ተከናውኗል።

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ ለዑለማዎች ምርጫ በአዳማ ከተማ ሁዳ መስጂድ ተገኝተው ድምጻቸውን መስጠታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ፕሬዚዳንቱ ባስተላለፉት መልእክት መጅሊሱ ጠንካራ ኢስላማዊ ተቋም ለመፍጠርና ህዝበ ሙስሊሙን ለማገልገል እየሰራ መሆኑን ገልጸው፤ የዛሬው ምርጫም ይህንኑ ዓላማ ያደረገ ነው ብለዋል።

ከዛሬ ጀምሮ እስከ ነሐሴ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የምሁራን፣ ወጣቶች ሴቶችና የስራ ማኅበራት ተወካዮች ምርጫ ይካሄዳል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከወረዳ እስከ ፌደራል ድረስ ሂደቱን ጠብቆ የሚካሄደው የመጅሊስ የምርጫ ነሐሴ 30 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2017 የምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ አስታውቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review