የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ 1 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የውጪ ምንዛሪ ክፍያ መፈጸሙን ገለጸ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ 1 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የውጪ ምንዛሪ ክፍያ መፈጸሙን ገለጸ

AMN ነሃሴ 10/2017

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በየጊዜው ለደንበኞቹ የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሪ በማቅረብ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት ለማስተናገድ እየሠራ መሆኑን አስታዉቋል።

ነሐሴ 10 ቀን 2017 ዓ. ም ለባንኩ የቀረቡ የውጭ ምንዛሪ የደንበኞችን ማመልከቻዎች መካከል ሁሉንም በማጽደቅ የ420.4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን የተለያዩ የውጭ ምንዛሪ ዓይነቶች ለተለያዩ ፍላጎቶች መፍቀዱን ባንኩ ገልጿል።

የተፈቀደዉ የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ ከሐምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ብቻ ከተፈቀደው ጋር ተደምሮ በአጠቃላይ ለባንኩ 1ሺ140 ደንበኞች 541.4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተመጣጣኝ የውጭ ምንዛሪ መፈቀዱን ጠቅሷል።

የተሰጠው የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ ከነዳጅ፣ ማዳበሪያ እና ሌሎች የአገልግሎት ክፍያዎች ጋር በተያያዘ በየቀኑ ከሚሰጠው መደበኛ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በተጨማሪ የተሰጠ ነው።

ባንኩ ከጁላይ 1 ቀን 2025 ጀምሮ ለገቢ ንግድና ለአገልግሎት ክፍያዎች በአጠቃላይ 1.034 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተመጣጣኝ የውጭ ምንዛሪ ክፍያ መፈጸሙን ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በላከዉ መረጃ አስታዉቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review