በኢንዶኒዢያ ሱላዌሲ ግዛት በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ 29 ሰዎች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፣ በ2 ሰዎች ላይ የከፋ ጉዳት መድረሱን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ገልጸዋል፡፡
በኢንዶኒዢያ ማዕከላዊ ሱላዌሲ በሀገሪቱ የሰዓት አቆጣጠር ዛሬ ማለዳ በተከሰተው እና በሬክተር መለኪያ 6.0 በሆነው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ፣ በርካቶች የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው የሀገሪቱ የአደጋ ቅነሳ ድርጅት አስታውቋል፡፡
የመሬት መንቀጥቀጡ ከ10 ኪሎ ሜትር ጥልቀት እንደተቀሰቀሰና ንዝረቱም በአቅራቢያ ባሉ አካባቢዎች መሰማቱን ድርጅቱ ገልጿል፡፡

በአደጋው 29 ሰዎች የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሲሆን፣ በሁለት ሰዎች ላይ የከፋ ጉዳት መድረሱንም ጨምሮ ጠቅሷል፡፡
እስከ አሁን የሞት አደጋ ስለመድረሱ የተገለጸ ነገር አለመኖሩን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ኢንዶኒዢያ ከመሬት መንቀጥቀጥ አንጻር በጣም ንቁ በሆነው እና የፓስፊክ የእሳት ቀለበት በሚባለው አካባቢ የምትገኝ ሀገር ናት፡፡
በታምራት ቢሻው