ከ100 ኪሎ ግራም በላይ ካናቢስ የተሰኘ አደንዛዥ ዕጽ በመኖሪያ ቤት ውስጥ ሸሽገው የተገኙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ

You are currently viewing ከ100 ኪሎ ግራም በላይ ካናቢስ የተሰኘ አደንዛዥ ዕጽ በመኖሪያ ቤት ውስጥ ሸሽገው የተገኙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ

AMN ነሃሴ 11/2017

ከ100 ኪሎ ግራም በላይ ካናቢስ የተሰኘ አደንዛዥ ዕጽ በመኖሪያ ቤት ውስጥ ሸሽገው የተገኙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የጉለሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለጸ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በተደረገ ፍተሻና ብርበራ

ነሐሴ 10 ቀን 2017 ዓ/ም በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው አጂብ ቶታል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ አንድ መኖሪያ ቤት በቁጥጥር ስር ዉለዋል።

አሸብር መኮንን እና ስብሀቱ አያሌው የሚባሉ ተጠርጣሪዎች ከ100 ኪሎ ግራም በላይ ካናቢስ የተሰኘ አደንዛዥ ዕጽ አምስት አምስት ኪሎ በሚይዡ ከረጢቶች በመጠቅለል ወደ ገበያ ለማቅረብ ሲያዘጋጁ እንደተያዙም ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ተጨማሪ ምርመራ የማስፋት ተግባሩን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ተገቢውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በማጠናቀር ክስ እንደሚያስመርት መግለጹን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በላከዉ መረጃ አስታዉቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review